ምርጫ ቦርድ እነ እስክንድር ነጋን በእጩነት ለመመዝገብ እንደሚቸገር አስታወቀ

0
551

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኹለተኛ ሰበር ሰሚ ችሎት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ቀለብ ስዩም እና አስካለ ደምሌ ለፓርቲው በዕጩነት ተመዝግበው መወዳደር እንደሚችሉ ውሳኔ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው ግንቦት 16/2013 በነበረው የችሎት ውሎው ነው።
በውሳኔው መሰረት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን በዕጩነት ለማስመዝገብ እና ፍርዱ እንዲፈጸም ለምርጫ ቦርድ በደብዳቤ የተጠየቀም ቢሆንም፣ ምርጫ ቦርድ ውሳኔውነ እንደማይፈጽም በደብዳቤ ምላሽ እንደተሰጠው ባልደራስ አስታውቋል።
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ዕጩ ተወዳዳሪ የሆኑት እነ እስክንድር ነጋን በተመለከተ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕጩ እንዳይሆኑ ሰጥቶት የነበረውን ውሳኔ በመሻር እንዲመዘገቡ ትዕዛዝ መስጠቱ ፓርቲው ጠቁሟል።
ይህን ተከትሎ ባልደራስ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚደርጉ ጠቁሟል።


ቅጽ 3 ቁጥር 134 ግንቦት 21 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here