በምርጫው ሂደት የሳይበር ጥቃት እንዳያጋጥም እየሰራ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ገለጸ

0
872

የምርጫ የሳይበር ደህንነት ሁኔታ ማረጋገጥ ማለት ምርጫንና የምርጫን መሠረተ-ልማቶች ከሳይበር ሥጋት ወይም ጥቃት መጠበቅ ማለት ነው። መረጃ ሰርሳሪዎች ይህም የምርጫ ጣቢያዎችን የምርጫ ማሽነሪዎች፣ የምርጫ ቁሳቁስ፣ የምርጫ ጽህፈት ቤት በይነ-መረብና መሠረተ ልማቶች እንዲሁም የመራጮች መረጃ ቋትን እንዳይበረበሩ፣ ሰርገው እንዳይገቡ ወይም ጉዳት እንዳይደርሱ መከላከል ነው።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ግዛው(ዶ/ር) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ከሚያስፈጽምባቸው ግብአቶች አንዱ የሚጠቀምባቸው ቴክኖሎጂዎችና የአሰራር ሥርዓቶች (ሲስተምስ) መሆናቸውን ገልጸዋል። በመሆኑም የምርጫ ባለድርሻ አካላት የሳይበር ምህዳር አጠቃቀማቸው ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ብለዋል።
በምርጫ ሂደቱ ቴክኖሎጂዎችና አሰራሮቹ ለሳይበር ጥቃት እንዳይጋለጡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ድጋፍና ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ለሳይበር ጥቃት ቢጋለጡና ሀገርና ህዝብን በእጂጉ ሊጎዱ የሚችሉ ተቋማትን በመለየት ኤጀንሲው በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ነው የተናገሩት። ከነዚህ ተቋማት አንዱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ምርጫ ቦርድ መሆኑንም ሹመቴ ገልጸዋል።
ዕጩ ተወዳዳሪዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ከምርጫው ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚገናኙ ተቋማት የሳይበር ጥቃት ኢላማ ሊሆኑ ስለሚችሉ እንዲጠነቀቁም መክረዋል። ቡድኑ በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ ወቅትና በድህረ ምርጫ ወቅቶች ሊያጋጥሙ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል ዝግጁ መሆኑንም ገልጸዋል።
በምርጫ ወቅት ሰርሳሪዎች የሳይበር ምህዳሩን ተጠቅመው ጥቃት ሊያደርሱ እንደሚችሉ በመገንዘብ ከግለሰብ እስከ ተቋም ያሉ ባለድርሻ አካላት ሁሉ በጥንቃቄና በኃላፊነት እንዲሰሩም ዋና ዳይሬክተሩ መክረዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 136 ሠኔ 5 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here