በሎጀስቲክስና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምርጫ ቦርድ ምክክር አካሄደ

0
400

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ሰኔ 02 ቀን 2013 ዓ.ም የምክክር መድረክ አከናውኗል። ከፓርቲዎች ጋር የተደረገው ምክክር በዋናነት ቦርዱ የድምጽ መስጫ ወረቀት ህትመትን አስመልክቶ ያጋጠመውን ተግዳሮት ለፓርቲዎች ሪፓርት ያቀረበበት ነው ተብሏል።
የእጩዎችን ቁጥር መሰረት አድርጎ በተደረገው የገንዘብ ድጋፍ ወቅት ፓርቲዎች የእጩዎች ቁጥር ላይ ባቀረቡት አቤቱታ፣ እንዲሁም በድምጽ መስጫ ወረቀት እና በውጤት ማሳወቂያ ፎርሞች መካከል የማስታረቅ ስራ ሲሰራ የተወሰኑ የምርጫ ክልሎች የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ላይ የተለያዩ ጉድለቶች መገኘታቸውን የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በሪፓርታቸው አሳውቀዋል። በዚህም መሰረት 54 የምርጫ ክልሎች ድምጽ መስጫ ወረቀቶች ድጋሚ ህትመት የሚያስፈልጋቸው ሆነው ተገኝተዋል።
በክልል ሲታይም
የቦርዱ ሰብሳቢ ለተፈጠረው ችግር በቦርዱ የተወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን አቅርበው በነዚህ ምርጫ ክልሎች የድምጽ መስጫ ወረቀቶችን አትሞ ለማድረስ የሚኖረውን ችግር በማንሳት እና በአጠቃላይ የሚያመጣውን የእሸጋ እና የስርጭት ተጽእኖ ካብራሩ በኋላ በነዚህ የምርጫ ክልሎች ድምጽ መስጫ ወረቀቶችን በድምጽ መስጫው ቀን ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት አስመልክቶ ፓርቲዎች ሃሳብ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።
ፓርቲዎች በስራ ላይ እንዲህ አይነት ችግሮች እንደሚያጋጥሙ ገልጸው የድጋሚ ህትመቱ በአገር ውስጥ የሚከወንበት እድል ቢታይ፣ አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ደሞ በጸጥታ የተነሳ ችግር ያጋጠመባቸው ቦታዎች ድምጽ በሚሰጡበት ወቅት አብረው የሚሰጡበት እድል መኖሩን እንደሌላ አማራጭ አቅርበዋል።
ችግሩን ለመፍታት ያሉትን ሁለት አማራጮች መሆናቸውን የተናገረው ቦርዱ አንደኛው አማራጭ የድምፅ መስጫ ወረቀቱን አገር ውስጥ ህትመት ማከናወን ሲሆን ሁለተኛው አማራጭ ደሞ ከላይ የተጠቀሱትን ምርጫ ክልሎች በጸጥታ ችግር የተነሳ ሰኔ 14 ቀን ድምጽ ከማይሰጥባቸው የምርጫ ክልሎች ጋር በጋራ ማከናውን ነው ብለዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 136 ሠኔ 5 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here