ከ 6 ወራት በፊት ጀምሮ በህብረት ባንክ ሲከናወን የነበረው የይቀበሉ ፣ ይመንዝሩ ፣ ይሸለሙ የሎተሪ መርሀ ግብር የዕጣ አወጣጥ ስነስርዐት ዛሬ ተካሂዷል ። ለባለ እድለኞች በሽልማት መልክ 1ኛ እጣ አቶሞቢል፣ 2ኛ እጣ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ፣ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ሽልማቶች ቀርበዋል።
በእጣ አወጣጥ ስነ ስርዓቱ ላይ የህብረት ባንክ የቢዝነስና ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ በተገኙበት የመጀመሪያ የሎተሪ እጣ አወጣት ተከናውኗል። በዚህም አንደኛ እጣ ቁጥር 924432 ፣ 2 እጣ ቁጥር 151777፣ 3 እጣ ቁጥር 131560 መሆናቸው ታውቋል፡፡



