ኢትዮጵያን ጨምሮ ዘጠኝ አገራት የተሳተፉበት የናይል ኢኳቶሪያል ኃይቆች የሚኒስትሮች ምክክር በአዲስ አበባ ተደርጓል፡፡
ኢትዮጵያ ለአንድ ዓመት ያህል በሊቀመንበርነት ስትመራው የቆየችው የቀጠናው የልማት ትብብር፣ አገራቱን የሚያስተሳስሩ የተለያዩ የኢነርጂ ሥራዎችን እንዳከናወነ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
በቀጠናው የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እና የድህነት ቅነሳ ላይ በአገራቱ መካከል በትብብር እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።
ቀጠናው በተፈጥሮ ሀብት የታደለ ሆኖ ሳለ በትብብር ከመስራት አንጻር ገና ብዙ ሥራ እንደሚጠበቅበት የሱዳን የመስኖና የውኃ ሃብት ሚኒስትር ያሲር መሐመድ መናገራቸውም ተዘግቧል።
ቅጽ 3 ቁጥር 139 ሠኔ 26 2013


