ከመተከል ዞን ተፈናቅለው የነበሩ ከ50 ሺሕ በላይ ዜጎች ይኖሩበት ወደነበረው ወረዳ ማዕከላት መመለሳቸው ተገለጸ።
ከ50 ሺሕ በላይ ከመተከል ዞን ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ይኖሩበት ወደነበረው ወረዳ ተመልሰው በተመረጡ ማዕከላት መኖር መጀመራቸውን የሰላም ሚኒስቴር ድጋፍና ክትትል ቡድን አረጋግጧል።
የሰላም ሚኒስቴር ከዞኑ ኮማንድ ፖስት፣ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ እና ከአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ በመሆን ከተፈናቃዮች ጋር ባደረጉት ተደጋጋሚ ውይይት ተፈናቃዮች ወደ ተዘጋጁላቸው ማዕከላት ተመልሰው አስፈላጊው ሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ተብሏል።
ተፈናቃዮች አሁን ላይ በአራት ማዕከላት ማለትም በቡለን ፣ ዳንጉር ፣ ማንዱራ እና ድባጤ ወረዳ መኖር ጀምረዋል።
የአካባቢው ነዋሪዎችም ወደ ማዕከላቱ ለተመለሱ ዜጎች ምግብና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ቅጽ 3 ቁጥር 139 ሠኔ 26 2013


