በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ መቀነሻ ዕቅድን ኢትዮጵያ አዘጋጅታ ለባለድርሻ አካላት አስተዋውቃለች።
እ.አ.አ በ2015 በፈረንሳይ ፓሪስ የተደረገውን ስምምነት ተግባራዊ ያደርጋል የተባለው ይህ ዕቅድ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስ ያስችላል በሚል ታምኖበት ነው ተብሏል።
ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ መቀነስ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየች መሆኑን የአካባቢ ደንና የአየር ንብርት ለውጥ ኮሚሽን ገልጿል።
እስከ 14 በመቶ በራስ አቅም እንዲሁም የውጭ አገራት የቴክኖሎጂና የገንዘብ ድጋፍ ካደረጉ ደግሞ እስከ 68 በመቶ የበካይ ጋዝ ልቀትን እ.አ.አ በ2030 ለመቀነስ ውጥን መያዙ በዕቅዱ መሰረት ተግባራዊ ለማድረግ መካተቱ ተነግሯል።
ቅጽ 3 ቁጥር 139 ሠኔ 26 2013


