አንጋፋ ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ዕድገት ፍኖተ ካርታ ላይ መምከራቸው ተገለጸ

0
818

በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሽልጣን አዘጋጅነት የአገራችን አንጋፋ ጋዜጠኞች ከሌሎች ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር በመሆን በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን እድገት ፍኖተ ካርታ ላይ መክረዋል።
የአገራችን መገናኛ ብዙኃን በአሁን ሰዓት በበርካታ እድሎች የታጀበ መሆኑን የጠቆሙት ተሳታፊዎቹ፣ የማህበረሰቡን ሥነ ልቦና እና በአገሪቱ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ በተቀናጀ መልኩ መሥራት ላይ ትልቅ ክፍተት እንደሚስተዋልም አክለው ገልጸዋል።
ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት መከበር ከተጀመረ ጊዜ ወዲህ የተሻለ እና የሚበረታታ ጠንካራ ሥራ ለመሥራት ትጋት ማሳየታቸው የማይካድ ቢሆንም፣ የአገራችን መገናኛ ብዙኃን በሰላም ግንባታ እና ዲሞክራሲን ከማዳበር አኳያ ገና ብዙ ሥራ እንደሚቀራቸው ዶክተር ንጉሴ ተፈራ ገልጸዋል።
በቀጥታ ከምዕራቡ አለም የተኮረጀ እና የአገሪቱን ሕዝቦች ባህል ፣ ትውፊት ፣ የኢኮኖሚ እና ሥነ ልቦና ደረጃ ያላገናዘበ አሠራር ውስጥ መግባት እንደ ቀላል መታለፍ ያለበት ጉዳይ እንዳልሆነ ከ50 ዓመት በላይ በጋዜጠኝነት እና በዲፕሎማሲ ሥራ ለይ ያገለገሉት አቶ ማዕረጉ በዛብህ አንስተዋል።
አሁን ላይ ያሉ ብዙ የፖለቲካ ሰዎች ሚዲያው እንዲሆን የሚሹት እና የሚዘውሩበት ርዕዮተ አለማዊ ሃሳብ ከሚድያ ገለልተኝነት መርህ አንፃር ምን ያክል ያራምድናል የሚለውን ጥያቄ ማጤን እንደሚያስፈልግ የሸገር ኤፍ ኤም ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ መዓዛ ብሩ አሳስበዋል።
የመገናኛ ብዙኃን የቋንቋ አጠቃቀም የማኅበረሰብን ክብር የሚጋፋ ከመሆኑም በላይ፣ ለማሻሻል ሙከራ ሲደረግ አለመታየቱ አሳዛኝ ነው ሲሉ ለ19 ዓመታት በኢትዮጵያ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት እና አሁን ላይ በኮሚዩኒቲ ዲቨሎፕመንት ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙት ወይዘሮ አባይነሽ ብሩ መናገራቸውን ከኢመብባ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።


ቅጽ 3 ቁጥር 139 ሠኔ 26 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here