የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው አጠቃላይ ምርጫ ድምፅ የመስጠት ሂደት ጋር ተያይዞ አቤቱታ ካቀረቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አካሄደ።
ቦርዱ ከቀናት በፊት ፖለቲካ ፓርቲዎቹ አቤቱታዎቻቸውን የሚያቀርቡበትን የመረጃ አቀራረብ ቅደም ተከተል ገምግሞል የትኞቹ ጉዳዮች አቤቱታ የሚቀርብባቸው እንደሆኑና በምን መንገድ መቅረብ እንዳለባቸው በይፋ መግለጹም ይታወቃል።
አቤቱታዎችን ለማደራጀትና ፓርቲዎቹ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁትን የመፍትሔ ሃሳቦች ሥርዓቱን ተከትሎ አደራጅቶ ለቦርዱ የሚያቀርብ የሕግ ባለሙያዎች ቡድን እንዳቋቋመም ተገልጿል።
በዚህም መሰረት ቦርዱ በአፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እንዲያመቸው ተመሳሳይ ስታንዳርድ ያለው የአቤቱታ ፎርም በማዘጋጀት እና የፓርቲዎችን አቤቱታ ከሚቀበሉ የህግ ባለሙያዎችን በማዘጋጀት ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
ቅጽ 3 ቁጥር 139 ሠኔ 26 2013


