ከውጪ ለገቡ ሰዎች የሚደረገው ጥበቃ የፌደራል ፖሊስን ማቋቋሚያ አዋጅ የሚጣረስ እንደሆነ ተገለጸ

Views: 539

በመንግስት ጥሪ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወደ ኢትዮጵያ ለገቡት ግለሰቦች መንግስት የሚያደርገው ጥበቃ ከፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ ጋር የሚጣረስ እንደሆነ የአዲስ በፌደራል ፖሊስ ሕግ ባለሙያ ኮማደር ፋሲል አሻግሬ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።

አክቲቪስት ጃዋር መሐመድን ጨምሮ ወደ አገር ውስጥ የገቡ ግለሰቦች ጥቃት ሊደርስባቸው ይችላል ተብሎ ጥበቃ ሲደረግላቸው የነበረ ሲሆን ይህም የፌደራል ፖሊስ ከተቋቋመበት አዋጅ ውጭ መሆኑን አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ ለግለሰቡ የሚደረገው ጥበቃ አስጊ ሁኔታ የለም ተብሎ በታሰበበት ወቅትም በማንኛውም ጊዜ ማንሳት እንደሚቻል አስታውቀዋል።

የፌደራል ፖሊስ ሲቋቋም ጥበቃ የሚደረግላቸውን ግለሰቦች የለየ ሲሆን እነዚህም መንግሥት አገርንና ሕዝብን ይጠቅማሉ ብሎ ኃላፊዎችን ሲሾም ኃላፊነቱ ቀጥታ የፖሊስ ኮሚሽን በመውሰድ ጥበቃ እንደሚያደርግ አመልክተዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com