ለኤችአይቪ ሕሙማን የሚሆን አዲስ የቲቢ መመርመሪያ በዛሬው ዕለት ይፋ መደረጉ ተገለፀ፡፡
መመርመሪያውን ወደ ስራ እያስገቡ ያሉት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የጤና ሚኒስቴር ከአጋር ተቋማት ጋር በመተባበር ነው።
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የኤችአይቪ ቲቢ ድርብ ጫና ካለባቸው 30 የዓለም ሀገራት አንዷ መሆኗ እና አዲሱ የመመርመሪያ ዘዴም ከዚህ ቀደም ከነበረው ውጤታማነቱ ከፍ ያለ እንደሆነ ተገልጿል።
አዲሱ የመመርመሪያ ዘዴ ከክልል የጤና ተቋማት ጋር በመሆን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች እንደሚተገበር ታውቋል።
TB LF-LAM የተባለውና በሽንት ናሙና ላይ የሚደረገው ይህ ምርመራ ጫናን እንደሚያቃልል የዘገበው ኢቢሲ ነው።



