በ800 ሚሊየን ብር ወጪ ለሚገነባው የሐዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ልህቀት ማዕከል የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ

0
572

በ800 ሚሊየን ብር ወጪ ለሚገነባው የሐዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ልህቀት ማዕከል የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።

የመሰረተ ድንጋዩን ያስቀመጡት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ሀገር የሚለወጠው በተማረና በሰለጠነ የሰው ሀይል መሆኑን ገልጸው፤ ለዚህም የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የጎላ ፋይዳ እንዳላቸው ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱም በሁለት ዓመት የሚጠናቀቅ መሆኑንና ለተለያየ ዘርፍ የሚውል በርካታ ክፍሎች ያሉት እንደሆነ ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር ዶክተር ሙሉ ነጋ የልህቀት ማዕከሉ የኢንቨስትመንት ፍሰቱን የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ እንደ ሀገር የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራትና ለቴክኖሎጂ ሽግግር ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በበኩላቸው በከተማዋ ትልልቅ ፕሮጀክቶችና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ አስተዳደሩ ጠንክሮ ይሰራል ያሉ ሲሆን ÷ከንቲባው የፕሮጀክቱን ዘርፈ ብዙ ጥቅም በመግለጽ ለፍጻሜው ከተማ አስተዳደሩ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

የሲዳማ ክልል የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አሻግሬ ጀምበሬ ፕሮጀክቱ ወደ ተግባር ሲገባ ለሀገር ችግር ፈቺና ተወዳዳሪ ዜጋን ለማፍራት የሚረዳ መሆኑን ከሃዋሳ ከተማ የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ያገኘነው ዘገባ ያመለክታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here