የወጣቶች አረንጓዴ አሻራ ተከላ መርሐ ግብር ተካሄደ

0
998

ኑ ኢትዮጵያን እናልብሳት የወጣቶች አረንጓዴ አሻራ ተከላ መርሐ ግብር ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት በተለያዩ ክልሎች መካሄዱ ተገለፀ፡፡

የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ማስጀመርያ ክልላዊ ፕሮግራም በአዊ ዞን በባንጃ ወረዳ በገምባሃ ቀበሌ በደመቀ ሁኔታ አካሂደዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመርያ ፕሮግራሙ በአዊ ዞን በባንጃ ወረዳ በገምበሃ ቀበሌ በርካታ ችግኞችን በመትከል የተጀመረ ሲሆን ማህበረሰቡ በአከባቢዉ ችግኞችን በመትከል የመሬትን ዘላቂነት እንዲያረጋግጥ እና እንዲንከባከብ እዉቀት እና ግንዛቤ እንዲኖረዉ አስችሏል ተብሏል።

በፕሮግራሙ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወጣት ጋሻዉ ተቀባ ተገኝተዉ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በክልል ደረጃ 4.5 ሚልዮን ወጣቶች የሚሳተፉበት 800 ሚልዮን ችግኝ ለመትከል አቅደዉ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ገልጸዋል።

ወጣት ጋሻዉ አያይዘውም የሚተከሉት ችግኞች የአከባቢ አፈርን የሚጠብቁ እና የአየር ጸባይን መልካምነት የሚያመጡ ብቻ ሳይሆኑ ለስራ እድል ፈጠራ የሚያገለግሉ መሆናቸዉን ገልጸዉ እንደ አማራ ክልል 1.8 ቢልዮን ችግኞች ወደፊት እንደሚተከሉም አስታዉቀዋል።

በፕሮግራሙ ከክልሉ ሁሉም ዞኖች የተወከሉ የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ አመራሮችና አባላት፣ ከፍተኛ የዞን እና የክልል አመራሮች፣ ከአዲስ አበባ ከተማ የተወከሉ ወጣቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች እንደተገኙበትም ታውቋል።

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ችግኝ ብቻ ሳይሆን ሰላም ፍቅርና ኢትዮጵያዊ አንድነትን አብረን የምንተክልበት እንዲሆን ለመስራት በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ በኦሮሚያ ክልልም ይኸንን የሚያጠናክር የማብሰርያ ፕሮግራም መጀመሩን ከብልጽግና ፓርቲ ፌስቡክ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here