የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

0
786

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለሁለት ዓመታት በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 104 ተማሪዎች አስመረቀ።

ተመራቂዎቹ በፌዴራል ስተዲስ፣ በሊደርሺፕ፣ በፒስ ኤንድ ኮንፍሊክት፣ በኮንፍሊክት ስተዲስ፣ በዴቬሎፕመንት ኮሙንኬሽን ኤንድ ሚዲያ እንዲሁም በፐብሊክ ፖሊሲ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸውም ታውቋል።

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ አባ-ገዳዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች መገኘታቸውን የኢ.ዜ.አ ዘገባ ያመለክታል።

ይህ በአዲስ መልክ የተዋቀረውን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ መርቀው መክፈታቸው የሚታወስ ሲሆን አካዳሚው በሱሉልታ ከተማ በአርባ ሄክታር መሬት ላይ የተገነባና አጠቃላይ የግንባታ ወጪው 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መሆኑም ይታወቃል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here