የክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና የሽኝት መርሀ-ግብር በመስቀል አደባባይ በዛሬው ዕለት ይከናወናል

0
590

‘የሺዎች እናት’ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና የቀብር ስነ-ስርዓት ዛሬ ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ በ9 ሰዓት በቅ/ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀም ታውቋል።

የክብርት ዶ/ር አበበች ስርዓተ-ቀብር ከመከናወኑ አስቀድሞ ከረፋድ 3 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ድረስ አባኮራን ሰፈር በሚገኘዉ መኖሪያ ቤታቸዉ የአስክሬን ሽኝት እንደሚካሄድ የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ገልጿል።

በመቀጠል ከቀኑ 5 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በመስቀል አደባባይ የክብር እንግዶች በሚገኙበት ለክብራቸዉ አሸኛኘት እንደሚደረግላቸዉ ኮሚቴው አስታውቋል።

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here