አዋሽ ባንክ በ2020/2021 የበጀት አመት 13.7 ቢሊየን ገቢ ማግኘቱን ተናገረ

0
1017
አዋሽ ባንክ በ2020/2021 የበጀት አመት 13.7 ቢሊየን ገቢ ማግኘቱን ተናገረ
አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ አመታዊ ተግባሩን ይፋ ባደረገበት መግለጫ ላይ እንዳሳወቀው፣ በበጀት ዓመቱ ያስመዘገበው 13.7 ቢሊዮን ገቢ ከአምናው የ3.5 ቢሊዮን ብር ብልጫ አሳይቷል።
በአመቱ ያገኘው ያልተጣራ ትርፍም 5.58 ቢሊየን ብር መሆኑ ተገልጿል።
ይህ መጠን ላለፉት 5 ዓመታት ይዞት የነበረውን ከግል ባንኮች አንደኛነቱን እንዲያስቀጥል አድርጎታል ተብሏል።
ባንኩ በዓመቱ ተቀማጭ ገንዘብን በ46% አሳድጓል የተባለ ሲሆን፣ በ2021 መጨረሻ የተከፈለ የካፒታል መጠኑም 8.2 ቢሊዮን መድረሱን አሳውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here