አንድ ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ ከ250 ዓመታት በፊት የታተመ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ ለቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለስልጣን አበረከተ

0
1276

ከዛሬ 250 ዓመታት በፊት የታተመና በአንድ ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ እጅ ላይ የነበረ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ ለቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለስልጣን ተበረከተ።

የ“ኪንግ ጀምስ ቅጂ” በመባል በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚታወቀው ቀደምት ሙሉ የእንግሊዘኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ ምንጮች አንዱ የሆነው እና በ1769 (እ.አ.አ) የታተመውን መጽሐፍ ቅዱስ ነዋሪነታቸው በአሜሪካን ዳላስ ቴክሳስ ያደረጉት የአቶ ሳምሶን መኮንን ጣሰው ባለቤት ወ/ሮ ቤተልሔም መኮንን ለቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለሥልጣን ማበርከታቸውን የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።

 አቶ ሳምሶን መኮንን መጽሐፉን በግሪጎሪያኑ የዘመን አቆጣጠር 2000 ዓ.ም አካባቢ በኢትዮጵያ የንጉስ ሰለሞንን የከበረ ማእድናት ፍለጋና ጥናት ላይ አብረዋቸው ይሠሩ ከነበሩ እንግሊዛዊ የሥራ ባልደረባቸው በስጦታ ያገኙት እንደነበረም ታውቋል።

 በርክክብ ስነስርዓቱ ላይም የኢፌደሪ ባሕል እና ቱሪዝም ሚንስቴር ዶ/ር ሒሩት ካሳው ፣ ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት የባሕል ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ፣ ዶ/ር ሙሉጌታ የቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ዋና ዳይሬክተር ተገኝተዋል።

ክብርት ሚኒስትሯም በርክክቡ ስነስርዓት የአቶ ሳምሶን መኮንን ቤተሰብ አርአያነት ያለው ተግባር ማከናወኑን ገልጸው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህንኑ አበርክቶ እንዲቀጥል በማሳሰብ ቅርሱን በይፋ ለቅርስ ጥናት እና ጥበቃ በማስረከብ ለአስረካቢዎቹም የተዘጋጀውን ሰርተፊኬት ከምስጋና ጋር ሰጥተዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here