ባለፉት ኹለት ዓመታት 1ሺሕ 183 ሰዎች በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ተከሰዋል

0
995

ከጥቅምት ወር 2011 እስከ ታህሳስ ወር 2013 ድረስ ብቻ 1ሺሕ 183 ሰዎች በሕገ-ወጥ መንገድ ሰዎችን ድንበር በማሻገር እና በሰዎች የመነገድ ወንጀል ተከሰዋል ተባለ። ከተከሰሱት ውስጥም 541 የሚሆኑት ጥፋተኛ ተብለው ቅጣት እንደተጣለባቸው የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተናግሯል። ተከሳሾቹ እንደየጥፋታቸው ክብደት ከ2 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ ጽኑ አስራት የሚደርስ ቅጣት እንደተላለፈባቸው ተሰምቷል። የቀሪ ተከሳሾች ጉዳይም በፍርድ ቤት ክርክር ሂደት ላይ እንደሆነ ተነግሯል። የፌዴራል እና የክልል ዐቃብያን ሕጎች እና ፖሊሶች ጥፋተኞችን ተከታትሎ በመያዝ እና የፍርድ ውሳኔ እንዲሰጣቸው በማድረግ ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል ተብሏል።
በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር እና በሰዎች የመነገድ ወንጀልን በማጋለጥ፣ ጥቆማ በመስጠትና የምስክርነት ቃል በመስጠት ዜጎች ትብብር ማድረጋቸው ተወሰቷል። በሕጋዊ መንገድ ከአገር ወጥቶ የተሻለ ገቢ ማግኘት የሰው ልጆች መሰረታዊ መብት ቢሆንም፣ በደላሎች በመታለል በሕገ- ወጥ መንገድ በመጓዝ ጉዳት የሚደርስባቸውና ሕይወታቸውን የሚያጡ ዜጎች አሁንም አሉ ያለው የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ጉዳዩ ካጋጠማችሁ ጠቁሙኝ ሲልም ጠይቋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 140 ሐምሌ 4 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here