1 ሺህ አንድ መቶ ሰባ አራት ካራት የሚመዝነው ይህ ግዙፍ አልማዝ በቦትስዋና ካሮዊ በተባለው የማዕድን ማውጫ የተገኝ ሲሆን ከዚሁ የማዕድን ማውጫ ከአንድ ሺ ካራት በላይ ክብደት ያላቸው አልማዞች ሲገኙ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው፡፡ የማዕድን ማውጫው ባለቤት የሆነው የካናዳው ኩባንያ ሉካራ ዳይመንድ ግዙፉን የከበረ ድንጋይ ለሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሞክግዌትሲ ማሲሲ ያቀረበ ሲሆን አልማዙ ቦትስዋና የግዙፍ አልማዞች መፍለቂያ መሆኗን ያስመሰከረ ነው ብሏል፡፡ ሲ ኤን ኤንም በዘገባው ከ2 አመት በፊት አንድ ሺ ሰባት መቶ ሃምሳ ስምንት ካራት የሚመዝነውና የአለማችን ሁለተኛው ግዙፍ አልማዝ በዚሁ ስፍራ መገኘቱን አስታውሷል፡፡



