ለኢትዮጵያ አንድነትና አብሮነት መስዋዕትነት ለሚከፍለው መከላከያ ሠራዊት ጎን እንቆማለን፡- ባለሀብቶች እና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት

0
724

ለኢትዮጵያ አንድነትና አብሮነት መስዋዕትነት ከሚከፍለው መከላከያ ሠራዊት ጎን እንቆማለን ሲሉ ባለሀብቶች እና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ገለጹ።

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከከተማዋ ባለሀብቶች እና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል ።

የመከላከያ ሠራዊት ትግራይን ለቆ የወጣው በፖለቲካ ውሳኔ መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትግራይ ህዝብ ህዝባችን ነው ለዚህም ወደ ልማቱ በመመለስ በማሰብ የተደረገ ነው ብለዋል።

ነገር ግን ሰላማዊ ህዝብን በመረበሽ አሸባሪውን የጁንታ ቡድን መደገፍ እንደማይቻል ገልጸዋል።

የከተማዋ ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም ለሠራዊቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ከንቲባዋ አሳስበዋል።

ባለሀብቱ የመከላከያ ሰራዊቱን በሚችለው አቅሙ ከመደገፍ ጎን ለጎን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በቦንድ ግዢም ሆነ በሌሎች ተግባራት የበኩሉን እገዛ ማድረግ እንዳለበት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ በበኩላቸው የመከላከያ ሰራዊት መርሁ ከራስ በፊት ለህዝብ ነውና ለህዝባችን ሠላም እና ለሃገራችን ዳር ድንበር በፅነት እንሰራል ብለዋል፡፡

የውትድርና ሥራ በወኔ ብቻ የሚሰራ አይደለም ያሉት ሌተናል ጀነራል ባጫ በትግራይ ያለው ጁንታ ህዝቡ ከሠራዊቱ ጋር እንዲዋጋ በማድረግ መንግስትን በዘር ማጥፋት ወንጀል ለመክሰስ በማሰብ እንደሆነም ተናግረዋል።

የህውሀት አሸባሪ ቡድን ተግባር በጥንቃቄ በመመልከት ህዝቡ ወደ ልቡ እንዲመለስ እድል ለመሰጠት በማሰብ ትግራይን ለቀናል ብለዋል ጄነራል ባጫ፡፡

ሀገር ከሁሉም በላይ ናት ያሉት በውይይቱ የተሳተፉ ባለሀብቶች ሀገር ስትኖር ብቻ ነው በሠልም ወጥተን እና ሠርተን መኖር የምንችለው በማለትም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ በሃገሩ ሁሉም ወተደር መሆን አለበት ሁሌም ለሠላማችን ዘብ መሆን አለብን፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሠላም ሠርቶና አትርፈን የተሻለ ህይወት እንዲኖር መከላከያው ለእኛ ደጀን እንደሆነው ሁሉ እኛም ከመከላከያ ጐን ልንቀም ይገባል ሲሉ ባለሀብቶቹ ገልጸዋል ።

ሰራዊቱ በሚፈልገው መንገድ በገንዘብም ሆነ በቁሳቁስ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ባለሀብቶቹ መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተሪ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here