በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ለአገራቸው ልማት አቅማቸው በፈቀደ ድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑ ተገለፀ

0
700

በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአገሪቱ ያለውን የኑሮ ውድነትና የተለያዩ ችግሮች እየፈተኗቸው ቢሆም በአገራችን የልማትና ሰብአዊ የድጋፍ ስራዎች አመርቂ ተሳትፎ ማድረጋቸውን በሱዳን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ገለጹ፡፡

በካርቱም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ በሱዳን ከሚገኙ የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ አመራር አባላት ጋር የ2013 የበጀት ዓመት የዲያስፖራ ዘርፍ የስራ አፈጻጸምን ገምግሟል።

ከዚህ አኳያ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 1.6 ሚሊዮን ብር ፣ ለገበታ ለሃገር ፕሮጄክት 1.7 ሚሊዮን ብር ፣ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ 1 ሚሊዮን ብር ፣ ለኮቪድ 19 መከላከያ 779 ሺህ ብር ፣ ለሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ከ217 ሺህ ብር በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ከ5.5 ሚሊዮ ብር ከዳያስፖራው መሰብሰቡ ተገልጿል፡፡

ከአገራዊ ፕሮጄክቶች ተሳትፎ ባሻገር 216 ኢትዮጵያውያን በግላቸውና በማህበር በመደራጀት በአገር ቤት በአነስተኛና መካከለኛ ኢንቨስትመንት እና የንግድ ሥራዎች ለመሳተፍ ተደራጅተው ወደ ሃገር እንዲገቡ ድጋፍ ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም 29 የዳያስፖራ ስብስቦችን ማጠናከር ተችሏል፡፡

በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መብታቸው ተከብሮና ጥቅማቸው ተጠብቆ እንዲኖሩና ለሚፈጸምባቸው የመብት ጥሰት የህግ ከለላ እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትኩረት ተሠርቷል፡፡ በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወደ ሱዳን ገብተው የታሰሩ 645 ዜጎቻችንን በማስለቀቅ ወደ አገራቸው እንዲገቡ ማድረግ መቻሉን ታውቋል፡፡

ከ2,600 በላይ ዜጎቻችን በራሳቸው ትራንስፖርት በመተማ በኩል ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ድጋፍ ተሠጥቷል፡፡ 6 ኢትዮጵያውያን ላይ የተጣለ የሞት ቅጣት ፍርድ አፈጻጸም እንዲዘገይና ጉዳያቸው በድጋሚ እንዲመረመር ጠበቃ በማቆም ለሕገ-መንግስት አጣሪ ፍርድ ቤት አቤቱታ እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡

በአሠሪዎቻቸው ደሞዛቸውን የተከለከሉ ዜጎች ጉዳይ ክትትል በማድረግ 181 ሽህ ብር እንዲከፈላቸው ማድረግ መቻሉ እና የአካል ጉዳትና ሞት የደረሳባቸውን ዜጎቻችን 141 ሽህ ብር ካሳ እንዲከፈላቸው ድጋፍ ተሰጥቷል፡፡

የተለያዩ ችግሮች የደረሰባቸውን ዜጎች ለማቋቋም 51 ሽህ ብር ከኤምባሲው ሠራተኞችና ግለሰቦች በማሰባሰብ ድጋፍ መደረጉም ተገምግሟል፡፡

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በበጀት አመቱ ከዲያስፖራ ጋር በተያያዘ የተከናወኑት ስራዎች ኤምባሲው ከኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራ አባላትና አደረጃጀቶች ጋር በመቀናጀት የተሰሩ መሆኑን ገልፀው፣ የዳያስፖራ አመራር አካላት ጊዜቸውንና ገንዘባቸውን ለማህበረሰቡ አገልገሎት በማዋል ላበረከቱት አስተዋጽኦ የምስጋና የምስክር ወረቀት መሰጠቱን ኤምባሲው ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here