በእያንዳንዱ ደቂቃ 11 ሰው በርሃብ ምክንያት ህይወቱ እንደሚያልፍ ኦክስፋም የተባለ የበጎ አድራጎት ድርጅት  ይፋ አደረገ

0
661

በአለም አቀፍ ደረጃ 155 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ ዋስትና ያልተረጋገጠላቸው እንደሆነና በእያንዳንዱ ደቂቃ 11 ሰው በርሃብ ምክንያት ህይወቱ እንደሚያልፍ የተገለፀ ሲሆን ይህ ቁጥር ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸርም 6 እጥፍ ጨምሯ ብሏል፡፡ ይህ አስደንጋጭ ቢሆንም  በጣም ከባድ የሚባል ህይወት እየመሩ ያሉ ሰዎች መኖራቸው መታሰብ ያለበት ጉዳይ እንደሆነም ጥናቱን ያደረገው ይህ ድርጅት ተናግሯል።ጦርነት ያለባቸው ሀገራት ለከፋ ርሀብ ከሚጋለጡት መካከል እንደሆኑ ሪፖርቱ አመላክቷል።ኦክስፋም 20 በጎ አድራጎት ድርጅቶች ተጣምረው ያቋቋሙት መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን በዋናነትም ድህነት ቅነሳ ላይ የሚሰራ ድርጅት ነው፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here