ባሳለፍነው ሳምንት ከ26/10/13 ዓ.ም እስከ 02/11/13 ዓ.ም ድረስ ከ 31 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ከሀገር ሊወጡ እና ወደሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆን የገቢ ኮንትሮባንድ 31 ሚሊዮን 059ሺ 580ብር፤ ወጪ ደግሞ 550ሺ 931 ብር ግምት እንዳላቸውም ተገልጿል፡፡
ከኮንትሮባንድ ቁሶቹ መካከል የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ሲጋራ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ፣ የሰው መድሀኒትና ሌሎችም ይገኙበታል።
በተጨማሪም ሶስት ተርጣሪዎች እና ታርጋ ቁጥር የሌላቸው አራት ሞተሮችን ጨምሮ 11 ተሽከርካሪዎች ኮንትሮባንድ ሲያዘዋውሩ መያዛቸውነ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡






