የቦይንግ ካምፓኒ ለተጎጂዎች ለመክፈል ቃል የገባውን የ5 መቶ ሚሊየን ዶላር ካሳ መክፈል ጀመረ

0
645

የቦይንግ ካምፓኒ ምርት የሆኑ ሁለት አውሮፕላኖች እ.ኤ.አ በ2018 በኢንዶነዢያ እንዲሁም በ 2019 ደግሞ በኢትዮጵያ በመከስከሳቸው አደጋ ለገጠማቸው ተጎጂ ቤተሰቦች ለመክፈል ቃል የገባውን የ5 መቶ ሚሊየን ዶላር የካሳ ክፍያ መስጠት መጀመሩ ተገለጸ፡፡

በሁለቱ በረራዎች ወቅት በደረሰ የመከስከስ አደጋ የ346 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡

እ.ኤ.አ በ2019 መነሻውን አዲስ አበባ በማድረግ ወደ ኬኒያ ሲበር በነበረው አውሮፕላን ላይ በደረሰው የመከስከስ አደጋ የ149 ሰዎች ህይወት ማለፉና ከነዚህ ውስጥም 32 ኬንያውያን እንደነበሩ ይታወቃል፡፡

የኬንያውያኑ ተጎጂ ቤተሰቦች በካምፓኒው ላይ መስርተውት የነበረውን ክስ ለማንሳት ፈቃደኛ በመሆናቸው የካሳ ክፍያው ባለፈው ሀሙስና አርብ ወደ እያንዳንዳቸው የባንክ አካውንት ገቢ እንደተደረገላቸው ታውቋል፡፡

ይህን የገለጹት ከ90 በላይ የአደጋው ተጎጂዎችን ጉዳይ በመያዝ በፍርድ ቤት ሲከራከር የነበረው የሪቤክ የህግ ቻርተርድ ሀላፊ ማኑኤል ቮን ናቸው፡፡

አደጋዎቹ ከተከሰቱ በኋላ የቦይንግ ካምፓኒ ከኤር ባስ ጋር ተወዳድሮ ትርፋማ እንዳይሆን ተጽዕኖ ውስጥ ወድቆ እንደነበር የሚታወስ ነው ሲል ኢዜአ ዘ ስታር የተሰኘውን የዜና ምንጭ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here