ኢትዮጵያና ሩስያ በወታደራዊ ቴክኒክ ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ በማተኮር ሲያካሂዱት የቆዩት ውይይት የተለያዩ ስምምነቶች ላይ በመድረስ ተጠናቋል

0
547

ኢትዮጵያና ሩስያ በወታደራዊ ቴክኒክ ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ በማተኮር ለ3 ቀናት ሲያካሂዱት የቆዩት ውይይት የተለያዩ ስምምነቶች ላይ በመድረስ ማጠናቀቃቸው ተገለፀ።

ለ11ኛ ጊዜ የተካሄደው ይህ ውይይት በ10ኛው የጋራ ውይይት ላይ የተደረሱ ስምምነቶች አተገባበርን በጥልቀት ተመልክቷል።

አሁን የተደረሰው ስምምነት የሁለቱን ሀገራት የቆየ ወዳጅነት ይበልጥ የሚያጠናክርና ይበልጥ በማቀራረብ አብሮ መስራት የሚያስችል መሆኑን በውይይቱ ማጠቃለያ ለይ የተገኙት የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ማርታ ሊዊጅ ገልፀዋል።

የሰራዊቱን አቅም በእወቀት ፣ በክህሎትና በቴክኖሎጂ ለማዘመን ለሚደረገው ጥረትም የሁለቱ ሃገራት ስምምነት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል።

በውይይቱም ከሩስያ ፌዴሬሽን ወታደራዊ ኃይል የቴክኒክ ዘርፍ የተለያዩ ተቋማትና ከኢፌዴሪ መከላከያ ልዩ ልዩ ክፍሎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት መሳተፋቸውን የመከላከያ ሰራዊት በማህበራዊ ድህረ ገፁ አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here