የህዳሴ ግድብ ጫናን የሚያወግዝ እና አምስት ሚሊዮን ሠልፈኞች ይሳተፉበታል የተባለ ሠልፍ ሊካሄድ ነው

0
602

የህዳሴ ግድብ ጫናን የሚያወግዝ እና አምስት ሚሊዮን ሠልፈኞች ይሳተፉበታል የተባለ ሠልፍ የፊታችን ሐምሌ 16 እንደሚካሄድ ተገለፀ።

“የኢትዮጵያ ተስፋ” በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄ የተገለፀው ይህ ሰልፍ የግድቡን ሁለተኛ ዙር ሙሌት ለመደገፍና ዓለም አቀፍ ጫናን የማውገዝ ዓላማን ሰንቆ እንደሚከናወንም ታውቋል።

ዩዝ ኔትወርክ ፎር ሴስቴኔብል ዴቨሎፕመንት የተሰኘ መንግስታዊ ያለሆነ ተቋም ከህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሄራዊ ም/ቤት ፅ/ቤት እና ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ ሰልፍ ላይም ከአምስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰልፈኞች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎችም በቀጣይ መሰል ሰልፎች እንደሚከናወኑ መርሀግበሩን ያሰናዳው ተቋም ለመገናኛ ብዙሃኖች በሰጠው መግለጫ ላይ መነገሩን ከአሻም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here