በትግራይ ክልል ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች የሚውል የመጀመሪያው ዙር የሰብዓዊ እርዳታ መቐለ መድረሱን የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።
መንግስት ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እርዳታ እንዲያቀርቡ ባቀረበው ጥሪ መሰረት ባሳለፍነው ሳምንት ከ40 የሚበልጡ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ ክልል መንቀሳቀሳቸው ይታወቃል፡፡
በዛሬው ዕለትም በክልሉ ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች የሚውል የመጀመሪያው ዙር የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች መቐለ መድረሳቸውን በዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት በትዊተር ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ በክልሉ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚውል 1 ሺህ ሜትሪክ ቶን የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል፡፡



