በአሜሪካ ውስጥ ብዙ የቦታ ስሞች አሁንም ዘረኝነት ይታይባቸዋል ተባለ

0
573

በአሜሪካ ውስጥ አሁንም የብዙ ቦታ መጠሪያ ስሞች ያለፈባቸው እና ዘረኛነት የሚታይባቸው እንደሆኑ ዛሬ ሲ ኤን ኤን ይዞት በወጣው ፅሁፍ ገልፅዋል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአሜሪካ ውስጥ የትምህርት ቤት እና የአካባቢ መጠሪያዎች የቃላቱ መነሻ ሊቀሰቅሱት የሚችሉት የዘረኝነት ስሜት ከግምት ውስጥ ገብቶ በድጋሚ እየታሰበባቸውና እየተቀየሩ ነው፡፡

ከእነዚህ መካከል ኔግሮ የሚል ቃል በውስጣቸው የያዙ የቦታ መጠሪያዎች ዋነኞቹ ናቸው፡፡የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ዳሰሳ ጥናት ዳታ ቤዝ እንደሚያሳየው ከሆነ ከ600 በላይ የሚሆኑ የቦታ ስሞች ኔግሮ የሚል ቃል ይዘው ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ስሞች በአንድ ወቅት በማህበረሰቡ ተቀባይነት የነበራቸው ቢሆንም አሁን ግን ፍፁም ተቀባይነት የሌላቸው እና አፅያፊ ስለሆኑ እየተቀየሩ ካሉት ውስጥ ናቸው፡፡ስማቸው ላይ ኔግሮ የሚል ቃል ያላቸው አካባቢዎች ጥቁሮች ይኖሩባቸው የነበሩ ቦታዎች ነበሩ፡፡እነዚህ ስሞች በሌላ አካባቢ ለሚኖሩ ሰዎችም ወደ እዚህ ቦታ አትምጡ የሚልን መልዕክት ሊይዙ ይችላሉ ተብሏል፡፡

በዚህ መሰረት በቴክሳስ ውስጥ 16 የሚሆኑ የቦታ መጠሪያዎች የተቀየሩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ኔግሮ ሄድ ሀይቅ የተባለውና አሁን ግን ሄነሪ ዶይል ሀይቅ የተባለው አንዱ ነው፡፡

ቨርማንት በተባለ ግዛት ውስጥም ነዋሪዎችና ፖለቲከኞች ኔግሮ ብሩክ የተባለው የቦታ ስም እንዲቀየር ግፊት እያረጉ ይገኛሉ፡፡ይህ ጉዳይ ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ የተነሳ ቢሆንም ነገሩ ትኩረት እንዲሰጠው ያደረገው ግን በባለፈው አመት ብላክ ላይቭስ ማተር በሚል ሲደረግ የነበረው ተቃውሞ እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡   

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here