ሁለት ኢትዮጵያውያን በደቡብ አፍሪካ ጥቃት ደረሰባቸው

0
596

የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት የጃኮብ ዙማን እስር ተከትሎ በአገሪቱ ሰላማዊ ሰልፎችና ነውጥ መቀስቀሱን ተከትሎ በጆሀንስበርግ የሚሠሩ ኢትዮጵያውያን ዛሬ መደብራቸውን ዘግተው እንደዋሉ በከተማዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊን ለቢቢሲ ተናገሩ።

በንግድ ሥራ የተሰማራው ዳዊት ተወልደመድኅን፤ በጆሀንስበርግ በተለይም ጂፒ ጎዳና እና ብሪ ጎዳና በሚባሉት አካባቢዎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ጥቃት እንዳይደርስባቸው ፈርተው ዛሬ ሐምሌ 5/2013 ዓ.ም. መደብራቸውን ዘግተው ለመዋል መገደዳቸውን ተናግሯል።

ትላንት ሐምሌ 4/2013 ዓ.ም. በዚያው አካባቢ በተነሳው ነውጥ የኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የሌሎች አገራት ስደተኞች መደብሮች ላይ ጥቃት ሲሰነዘር ፖሊስ እንደተከላከለ ዳዊት ይናገራል።

በደቡብ አፍሪካ የተባበሩት ኢትዮጵያ ማኅበሰረብ ማኅበር ዋና አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የሆነው ንጉሥ ተመስገን እንደሚናገረው ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያን፣ ፓኪስታናውያን እንዲሁም ሌሎችም የሚነግዱበት አካባቢ ዛሬ ተዘግቶ ውሏል።

“ሁለት ኢትዮጵያውያን ጥቃት ደርሶባቸዋል። ከባድ ግን አይደለም። ዛሬ ሶዌቶ አካባቢ አመጽ ስላለ በንግድ የተሰማራው የሀበሻው ማኅበረሰብ ሱቁን ዘግቷል። ደርባን ትላንት ሌሊት ሲዘረፍ፣ መኪና ሲቀጠል ነበር” ብሏል።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here