‘ሰልፊ’ ሲነሱ የነበሩ 11 ሰዎች በመብረቅ ተመተው ሕይወታቸው አለፈ

0
712

በሕንድ ሰሜናዊ ጃዩፐር በተባለች ከተማ እራሳቸውን ፎቶ ሲያነሱ የነበሩ 11 ሰዎች በመብረቅ ተመተው ሕይወታቸው አለፈ።

በትናንትናው ክስተት ከሟቾቹ በተጨማሪ ሌሎች በርካቶች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።

ከባድ ዝናብ እየጣለ ሳለ ነበር ሟቾቹ አመር ፎርት የሚባሉ የቱሪስት መዳረሻ ማማ ላይ ራሳቸውን ፎቶ እያነሱ በከፍተኛ መብረቅ የተመቱትና ሕይወታቸው ያለፈው።

አደጋው ሲከሰት በማማው ላይ 27 ሰዎች የነበሩ ሲሆን የተወሰኑት ከማማው ላይ በመዝለል ሕይወታቸውን ታድገዋል ተብሏል።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here