በአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ በተጠረጠሩት ግለሰቦች ላይ የመከላከያ ምስክሮችን መስማት ጀመረ

0
1028

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰኔ 15/2011 ዓ.ም በአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ በተጠረጠሩት በእነ ሻምበል መማር ጌትነት መዝገብ የተከሰሱ 32 ተከሳሾችን የመከላከያ ምስክሮች ዛሬ መስማት ጀመረ።

ፍርድ ቤቱ በእነሻምበል መማር ጌትነት የክስ መዝገብ የክስ ሂደታቸውን ሲከታተሉ ከቆዩ 55 ተከሳሾች መካከልም 20ዎቹ ሰኔ 11/2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ መደረጉ ይታወሳል።

በዋና ወንጀል ፈጻሚነት በሌሉበት ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው ሲታይ የቆየው አንደኛ ተከሳሽ ሻምበል መማር ጌትነት፣ 15ኛ ተከሳሽ በላይነው ሰፊነው እና 44ኛ ተከሳሽ ልቅናው ይሁኔ ላይ ደግሞ ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ፍርድ መስጠቱ ይታወቃል።

ይህም በወንጀል ድርጊቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ ሆነው መገኘታቸው በሰውና በአቃቤ ህግ ማስረጃ በመረጋገጡ እንደሆነ በወቅቱ ተገልጿል።

የቀሩት 32 ተከሳሾች ደግሞ እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ለሐምሌ 5/2013 ዓ/ም በሰጠው ቀነ ቀጠሮ መሰረት የተከሳሾችን የመከላከያ ምስክሮች ቃል ዛሬ መስማት ጀምሯል።

የተከሳሽ ጠበቆች ያቀረቧቸው አብዛኞቹ የመከላከያ ምስክሮች በተመሳሳይ ወንጀል የተከሰሱ በመሆናቸው እንዳይመሰክሩ ህጉ ስለሚከለክል የመከላከያ ምስክር ሆነው ሊቀርቡ አይችሉም የሚል መቃወሚያ አቃቤ ህግ አቅርቧል።

የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ፤ አንደኛው ተከሳሽ ለሌላኛው ተከሳሽ እንዳይመሰክር የሚከለክል ህግ የሌለ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ያቀረበውን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ የቀረቡ የመከላከያ ምስክሮችን እንዲሰማ ሲል ተከራክሯል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here