የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለፋሲል ከነማ የስፖርት ቡድን ዲጂታል የመረጃ አስተዳደር (ፖርታል) ሊያለማለት መሆኑን አስታወቀ

0
778

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለፋሲል ከነማ የስፖርት ቡድን ዲጂታል የመረጃ አስተዳደር (ፖርታል) ሊያለማለት መሆኑን አስታወቀ።

ዲጂታል የመረጃ አስተዳደሩ የፋሲል ከነማ የስፖርት ቡድንን መረጃ ለደጋፊዎቹና ለማህበርሰቡ ባሉበት ለማድረስ የሚያስችል ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ (ፒ ኤች ዲ) ከፋሲል ከነማ የስፖርት ቡድን ስራ አስኪያጅና የቦርድ አመራሮች ጋር ቡድኑን የዲጂታል ፖርታል ባለቤት ማድረግ በሚቻልበት ዙሪያ መክረዋል።

ዲጂታል የመረጃ አስተዳደሩ ከፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ሊንክድኢን ከመሳሰሉ ማህበራዊ ሚዲያዎችና ከቴሌ ብር ጋር በማገናኘት አገልግሎት መስጠት የሚያስችልም እንደሆነ ታውቋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ታሪካዊውን የፋሲል ከነማ የስፖርት ቡድን ዲጂታል የመረጃ አስተዳደር በአንድ ወር ጊዜ አልመተን እናስረክባለን ብለዋል።

እንደ ሀገር የተጀመረውን የዲጂታል ጉዞ ወደ ሁሉም ዘርፎች ለማውረድ እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።

የፋሲል ከነማ የስፖርት ቡድን ስራ አስኪያጅ አቶ አብዮት ብርሃኑ ባለሙያዎችን በማሟላት የመረጃ አስተዳደሩ ሳይቆራረጥ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ዲጂታል የመረጃ አስተዳደር ስርዓቱ የክለቡን ታሪክ፣ ዕለታዊ የእንቅስቃሴ መረጃ፣ የገቢ ማስገኛ ሽያጭ፣ የደጋፊዎች መረጃ፣ ድጋፍ ማሰባሰቢያና የመሳሰሉትን መረጃዎች አስተሳስሮ እንደሚይዝ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here