ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 6 ዜጎች ወደ ሃገራቸው ተመለሱ

0
931

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ በተያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ዜጎች በየቀኑ ወደ ሃገራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።

በዚህ መሰረት በትናንትናው ዕለት 633 ሴቶችንና 248 ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ሺህ 6 ዜጎች ወደ ሃገራቸው ገብተዋል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን ያቀፈው ኮሚቴ ተገቢው አቀባበል እንዳደረጉላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here