የውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ የፀጥታው የምክር ቤት አባላት የኢትዮጵያን የልማት ስራዎች በመገንዘብ ጉዳዩ ወደ አፍሪካ ህብረት እንዲመለስ መደገፋቸውን እንደሚያደንቁ አስታወቁ።
ኢትዮጵያ እንደ ተለመደው ሁሉን አቀፍ እና ሁሉም አሸናፊ በሚሆንበት መንገድ ለመደራደርና ሂደቱንም ለመቋጨት ዝግጁ ነች ብለዋል፡፡
ሀገሬ ኢትዮጵያን ወክለን በመቅረብ እውነቱ በመገለጡ የተሳካ ውጤት አግኝተናል ያሉት ሚንስትሩ ኢትዮጵያ መፍትሄው በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት በድርድር ይፈታል እንጂ የደህንነት ስጋት አድርጎ በመሳል በዓለም አቀፍ አካላት ሊታይ አይገባም ብላ ታምናለች ሲሉ መልእክት ማስተላለፋቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።



