በቀን ከ 1.2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በአዲስ አበባ ትራንስፖርት አገልግሎት እያገኙ አይደለምተባለ

0
628

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አረጋዊ ማሩ ከኢትዮ FM 107. 8 ጋር በነበራቸው ቆይታ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ከሚፈልገው 4 ሚሊዮን ዜጋ ውስጥ አገልግሎቱን የሚያገኘው 2.73 ሚሊዮን ያህሉ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

አቶ አረጋዊ አንደተናገሩት ከሆነ  መንግስት የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞችን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የፐብሊክ ሰርቪስ አቋቁሞ 430 አውቶብሶች አገልግሎት እንዲሰጡ ቢደረግም የትራንስፖርት እጥረቱን ማቃለል አልተቻለውም ብለዋል፡፡

በከተማዋ የትራንስፖርት እጥረት እንዲከሰት በማድረግ የአገልግሎት መስተጓጎል የሚፈጥሩ አካላት ላይ አስተማሪ እርምጃ ባለመወሰዱ ችግሩ ተባብሶ ቀጥሏል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አቶ አረጋዊ የአገልግሎት መስተጓጎል የሚፈጥሩ አካላት ላይ ቅጣቱን አጠንክረን ለመጣል እየሰራን ያሉ ሲሆን ለአንዱ ባስ 7 ሚሊዮን ብር አውጥተን የገዛናቸው 100 ዘመናዊና ጥራታቸውን የጠበቁ ባሶች ወደ አገልግሎት ሲገቡ የትራንስፖርት ችግሩን በተወሰነ መልኩ ያቃልሉታል ብለን እናምናለን ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የትራንስፖርት እጥረት ችግሩን ለማቃለል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች አገልግሎት እንዲሰጡ አድርጓል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here