በመንግስት በአሸባሪነት የተፈረጀው የህወሃት ቡድን ህጻናትን በጦርነት ማሰማራቱን የሚገልጹ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ

0
670

የኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት የተፈረጀው የህወሓት ቡድን ህጻናትን በጦርነት ማሰማራቱን የሚገልጹ መረጃዎች እየወጡ መሆናቸው ተገለፀ።

በቅርቡ መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ክልል መውጣቱን ተከትሎ የህውሃት ቡድኑ የደረሰበትን ሽንፈት የሰው ዋጋ በመክፈል ለመመለስ እየተፍጨረጨረ እንደሆነም ተጠቁሟል።

ቡድኑ ህጻናት ወታደራዊ ስልጠና እያገኙ በጦርነት እንዲሰማሩ የሚያደርግ አስገዳጅ ድርጊት በመፈፀም፤ ህጻናትን ለጦርነት በግልጽ እያሰማራና ዓለም ዓቀፍ ወንጀል እየፈጸመ ስለመሆኑ ኒው ዮርክ ታይምስ ባወጣው ዘገባ ላይ አስታውቋል።

ከዘገባው ጋርም ህጻናት የጦር መሳሪያ ተሸክመው ሲንቀሳቀሱ የሚያሳይ ፎቶ አያይዞ አውጥቷል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here