በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን በታላቁ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር እንደገና ለማስጀመር ኢትዮጵያ ያላትን ቁርጠኝነት አስታወቀች

0
424

በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት የሚመራው የሶስትዮሽ ድርድርን እንደገና ለማስጀመር ኢትዮጵያ ያላትን ዝግጅት እና ቁርጠኝነት የሚያመለክት ጋዜጣዊ መግለጫ የኢፌድሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አውጥቷል።

በመግለጫውም ላይም በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሶስትዮሽ የድርድር ሂደት በጋራ ተቀባይነት ያለው ውጤት ለማምጣትና ስኬታማ መደምደሚያ ላይ ለመድረስ ስለሚያስችል በኢትዮጵያ በኩል ለድርድሩ ቁርጠኝነትና ከፍተኛ ተነሳሽነት መኖሩ ተገልጿል።

የህዳሴ ግድብ ድርድር ወደ መንግስታቱ ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት መወሰዱም ተገቢ እንዳልነበር በመግለጫው ተካቷል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር በቀረበው የደረጃ አካሄድ ላይ ለመስራት ዝግጁ በመሆኗ ግብፅም ሆነ ሱዳን ሂደቱን ወደ ፍሬ ለማምጣት በቅን ልቦና እንዲደራደሩም የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚያበረታታ ተገልጿል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here