በአዲስ አበባ ከተማ ከአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

0
1205

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ከ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ከተማ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል። ይህም የእቅዱ አፈጻጻም መቶ ስድስት በመቶኛውን ማሳካት እናዳስቻለው ተነግሯል::

ተቋሙ ለስራ ማስኬጃ ሁለት መቶ ሰላሳ ስምንት ሚሊየን ሀለት መቶ ሰባ ስምንት ሺህ አምስት መቶ ዘጠና ስድስት ብር በጀት የተመደበለት ሲሆን ብር ሁለት መቶ ሀያ ሚሊየን ሁለት መቶ ዘጠና አራት ሺህ ሶስት መቶ አርባ ስራ ላይ አውሏል፡፡ ይህም የበጀት አጠቃቀም ዘጠና ሁለት ነጥብ አርባ ሁለት በመቶ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ባለስልጣኑ የ2013 የበጀት አመትን አፈጻጸም በተመለከተ ግምገማ ባካሄደበት ወቅት እንደተገለፀው በዓመቱ ለ 15 ሺህ ተሽከርካሪዎች ድንገተኛ የመንገድ ላይ ምርመራ ለማከናወን ታቅዶ 11 ሺህ 775 መከናወኑ ታውቋል።

ምርመራ ከተከናወነባቸው ተሽከርካሪዎች መካከል 7 ሺህ 801 የሚሆኑት የቴክኒክ ጉድለት ሳይገኝባቸው ምርመራውን በብቃት ማለፋቸው ተነግሯል።

27 ተሽከርካሪዎች መጠነኛ የቴክኒክ ጉድለት ያለባቸው እና ያለቅጣት ችግሩን በ 5 ቀናት ውስጥ አስተካክለው እንዲቀርቡ መደረጋቸውንና 3 ሺህ 967 ከባድ ጉድለት ያለባቸው ደግሞ ተቀጥተው የቴክኒክ ጉድለት አስተካክለው እንዲቀርቡ መደረጉም ተጠቅሷል።

ባለስልጣኑ በሰጣቸው የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ አገልግሎቶችም በበጀት ዓመቱ 1 ቢሊዮን 693 ሚሊዮን 184 ሺህ 864 ብር ገቢ ተገኝቷል ሲል አስታውቋል፡፡

ይህም የእቅዱ 106 ነጥብ 3 በመቶ አፈጻጻም መሆኑ ነው የተገለጸው::

ገቢው የተገኘው የአሽከርካሪና የተሽከርካሪ ፍቃድ በማደስና በመስጠት እንዲሁም የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ አገልግሎትን በመስጠት መሆኑ ተገልጿል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here