በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አስተዳደር በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ5 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገለጸ፡፡
የወራቤ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ አደጋ መከላከል ቁጥጥር ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ ምክትል ሳጅን ቢላል አወል ዛሬ ከረፋዱ 5 ሰዓት ገደማ ካሊድ ወንዝ ላይ ኤፍኤስ አር ሲኖ ትራክ እና ባለሶስት እግር ባጃጅ ተጋጭተው አደጋው አደጋው መድረሱን አስታውቀዋል።
በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ5 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።
የአደጋው ተጎጂዎች በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን አስተባባሪው መናገራቸውን ከደቡብ ክልል መንግሥት ኮሚሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።




