በአዲስ አበባ ከ900 በላይ ለሆኑ አርሶ አደሮች የማዳበሪያና ምርጥ ዘር ድጋፍ ተደረገ

0
861

በአዲስ አበባ ከተማ ከ900 በላይ ለሆኑ አርሶ አደሮች የማዳበሪያና ምርጥ ዘር ድጋፍ መደረጉ ተገለፀ።

ለአርሶ አደሮቹ ድጋፍ ያደረገው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦሌ ክፍለ ከተማ የ2013/14 ምርት ዘመን የመኸር እርሻ ስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ለአርሶ አደሮችና መስራት ለማይችሉ አቅመ ደካሞች የተለያዩ ድጋፎችንም የደረገ ሲሆን ለ934 የከተማ አርሶ አደሮች የማዳበሪያና ምርጥ ዘር ድጋፍ ሲያደርግ ለ290 አቅመ ደካሞች ደግሞ ብርድ ልብስና አንሶላዎችን አበርክቷል።

የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መኮንን አምባዬ በመዲናዋ ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች የመሬት ማረጋገጫ ደብተር እየተሰጣቸው መሆኑን ተናግረዋል።

“በመሆኑም አርሶ አደሩ መሬቱን ከመሸጥ ይልቅ በመሬቱ ላይ ሰርቶ እንዲጠቀም በማሳሰብ በኢኮኖሚ ራስን ለመቻል ሁላችንም መታገል አለብን” ሲሉ መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here