ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ  መሰብሰቡ ተገለጸ

0
674

በ2013 በጀት ዓመት ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ከህዝብ መሰብሰቡን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

ከሐምሌ 1/2012 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 /2013 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ለግድቡ 2 ቢሊዮን 49 ሚሊዮን 85 ሺህ 105 ብር ከህዝብ መሰብሰቡን የፅህፈት ቤቱ የህዝብ ግንኙነት የሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብርሃም በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል።

ከሀገር ውስጥ ቦንድና ስጦታ 1 ቢሊዮን 767 ሚሊዮን 383 ሺህ 208 ብር የተሰበሰበ ሲሆን ከውጭ ሀገር ዲያስፖራ ቦንድ ሽያጭ እና ስጦታ 134 ሚሊዮን 96 ሺህ 860 ብር መገኘቱንም ኃላፊው ገልጸዋል።

በተጨማሪም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከ8100 አጭር የሞባይል መልእክት አገልግሎት 132 ሚሊዮን 853 ሺህ 752 መቶ ብር መገኘቱንም አቶ ኃይሉ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት የግድቡ ሁለተኛ ዙር ሙሌት እየተካሄደ ሲሆን አሁን ያለውን የህዝብ ተነሳሽነት ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ እንዲውል የተለያዩ እቅዶች ተነድፎ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ እስካሁን ከህዝብ የተሰበሰበው የገንዘብ ድጋፍ 15 ቢሊዮን 729 ሚሊዮን ብር በላይ መድረሱን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ምክር ቤት አስታውቋል ሲል የዘገበው ኢቢሲ ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here