የሲሚንቶ ግብይትን የሚወስነው እና በንግድና ኢንዱስትሪ ተግባራዊ ሲሆን የቆየው መመሪያ መሻሩን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሚኒስቴሩ የንግድና እቃዎች ጥናትና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ሙላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰ ጊዜ ሲሚንቶ በነፃ ገበያ ስርዓት እንዲገበያይ መወሰኑን አስታውቀዋል።
ለዚህም ዋና ምክንያት ክረምት በመሆኑ የግንባታ ስራዎች ስለሚቀንስና ከእዚህም ጋር ተያይዞ የሲሚንቶ ምርት ፍላጎት ስለሚቅንስ፤ እንዲሁም ከፋብሪካዎች ጋር ችግሩን ለመፍታት ስምምነት ላይ በመደረሱ መሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የሲሚንቶ ምርት እጥረት እንዳይኖር መንግስት ከውጪ ለማስገባት ዝግጅት ማጠናቀቁና ፋብሪካዎች ምርታቸው እንዲጨምር በመደረጉ መሆኑን አቶ ካሳሁን አብራርተዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።



