የአማራ ክልል መንግስት በተለያዩ ወቅቶች ሰልጥነውና አገልግለው በአሁኑ ወቅት በሌላ የሙያ ዘርፍ ላይ ለሚገኙ የቀድሞ የጸጥታ አካላት ጥሪ አቀረበ

0
727

የአማራ ክልል መንግስት ከዚህ በፊት በተለያዩ የጸጥታ መዋቅር ውስጥ ሲያገለግሉ ቆይተው በአሁኑ ወቅት በሌላ ዘርፍ ለሚገኙ የክልሉ ነዋሪዎች የአማራ ህዝብ ለተደቀነበት የህልውና አደጋ ሲሉ የጸጥታ መዋቅሩን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቀረበ።

የክልሉ መንግስት ባወጣው መግለጫ “በየትኛውም ዘመን ሰልጥናችሁ፣ የአገርና የህዝብ ሉአላዊነት ለማስከበር በማንኛውም የመንግስት ጸጥታ መዋቅር ውስጥ ተሰልፋችሁ ስታገለግሉ የቆያችሁና በታሪክ አጋጣሚ የሙያ ዘርፍ የቀየራችሁ የክልላችን ነዋሪዎች ለህልውናችን የምናደርገውን የትግል ጥሪ ተቀብላችሁ በክልሉ ጸጥታ መዋቅር ውስጥ እንድትቀላቀሉ ጥሪያችንን እያቀረብን ከዛሬ ጀምሮ በየአካባቢያችሁ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት በአካል ተገኝታችሁ በፈቃደኝት እንድትመዘገቡ ለማሳሰብ እንወዳለን” ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንም ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባወጣው መረጃ ሻለቃና ከሻለቃ ማእረግ በላይ ማዕረግ ያላቸው ከፍተኛ መኮንኖች በክልሉ ሰላምና ደህንንት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 313፤ ከሻለቃ በታች ማዕረግተኛ የሆኑ ደግሞ በያሉበት ዞንና ወረዳ የሰላምና የህዝብ ደህንነት ቢሮዎች እየቀረቡ እንዲመዘገቡ ጥሪ ማቅረቡም ታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here