ክቡር አምባሳደር ሐሰን ታጁ በኩዌት የሙባረክ አል-ከቢር ግዛት ዋና አስተዳዳሪ ጋር ተወያዩ

0
553

በውይይታቸውም ዋና አስተዳዳሪው የዜጎች ደኅንነትን በሚመለከት በግዛት ክልሉ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ጥበቃና ድጋፍ እንደሚያደርጉና ከኤምባሲው ጋር በትብብር እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

በኩዌት የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሐሰን ታጁ ሐምሌ 7 ቀን 2013 ዓ.ም በኩዌት የሙባረክ አል-ከቢር ግዛት ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር መሐመድ አብዱልሰመድ ቡሻሪ ጋር በጽ/ቤታቸው በመገኘት በተለያዩ የጋራ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

በዚህ ወቅት ክቡር አምባሳደሩ በሁለቱ አገራት መካከል መልካም ግንኙነት መኖሩን ጠቁመው፣ በግዛት ክልሉ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ለሚያደርጉት ድጋፍ ዋና አስተዳዳሪውን አመስግነዋል። በዚህ ረገድ ያለው ትብብርም ተጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ኢምባሲው አስታውቋል።

በተጨማሪም ክቡር አምባሳደር ሐሰን ኢትዮጵያ ባሏት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለያዩ ዘርፎች የሰለጠኑ በርካታ ባለሙያዎችን በየዓመቱ እንደምታስመርቅ ጠቁመው፣ ከቤት ሰራተኞች ባሻገር በፕሮፌሽናል የሰራተኞች ስምሪት ዘርፍ ከኩዌት ጋር በትብብር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።

ዋና አስተዳዳሪው በበኩላቸው በክቡር አምባሳደሩ የተነሳውን ሃሳብ እንደሚደግፉ ጠቁመው፣ የዜጎች ደኅንነትን በሚመለከት በግዛት ክልሉ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ጥበቃና ድጋፍ እንደሚያደርጉና ከኤምባሲው ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here