በቼክ ሪፐብሊክና ኢትዮጵያ መካከል በኢንቨስትመንት ዙሪያ የስራ ጉብኝ ለማድረግ ስምምነት ላይ ተደረሰ

0
728

በቼክ ሪፐብሊክና ኢትዮጵያ መካከል በኢንቨስትመንት ዙሪያ የስራ ጉብኝ ለማድረግ ስምምነት ላይ መደረሱ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በኢትዮጵያ የቼክ ሪፐብሊክ ኢምባሲ ኮመርሺያል ካውንስለር ፓቨል ሳራን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

በውይይታቸውም ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማጠናከር በሚቀጥለው ህዳር ወር ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ እያከናወነች ያለውን ስራ ለመጎብኘት የቼክ ሪፐብሊክ ልዑክ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የስራ ጉብኝት ለማድረግ  ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here