የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በ2013 በጀት ዓመት ከ19 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ለስኳር ህክምና አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን ማስራጨቱን የስርጭት ቡድን መሪ አቶ ተስፋሁን አብሬ ገለጹ፡፡
የተሰራጩት መድኃኒቶች ለአይነት 1 እና 2 (Type 1 and 2) የስኳር ህሙማን ህክምና አገልግሎት የሚውሉ ሲሆን 1 ሚሊየን 887 ሺህ 425 እሽግ ለ ጤና ተቋማት መሰራጨቱን አቶ ተስፋሁን ተናግረዋል፡፡
ስርጭቱም በአዳማ፣በአርባ ምንጭ፣ በአሶሳ፣ በባህርዳር፣ በደሴ፣ በጋምቤላ፣ በድሬደዋ፣ በጎንደር፣ በሀዋሳ፣ በጅጅጋ፣ በመቀሌ፣ በነገሌ ቦረና፣ በነቀምት፣ በሰመራ፣ በሽሬ፣ በአዲስ አበባ ቁጥር 1 እና 2 ቅርንጫፎች አማካኝነት የተሰራጨ ሲሆን 19 ሚሊየን 880 ሺህ 338 .68 ብር ወጪ እንደተደረገባቸው ቡድን መሪው አስረድተዋል ሲል ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡





