የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ከአሜሪካ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ካሮሊን ራያን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው ወቅትም በኤች ኤይ ቪ ኤድስ፣ በክትባት፣ ለህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ ምላሽ መስጠት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ማድረጋቸውን ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡
በተጨማሪም የላቦራቶሪዎችን አቅም ማሳደግ እንዲሁም አዳዲስ ትብብር ማድረግ በሚቻልባቸው የጤና መስኮች ዙሪያ መምከራቸውንም አስታውቀዋል።



