የቦሌ ሊሚ ኢንደስትሪ ፓርክ የኢንቨስተሮች ማህበር አባላት በኢንቨስትመንት ኮሚሽን ውይይትና ጉብኝት አደረጉ

0
544

የቦሌ ሊሚ ኢንደስትሪ ፓርክ የኢንቨስተሮች ማህበር አባላት ዛሬ ከኮምሽነር ለሊሴ ነሜ እና ከምክትል ኮምሽነር ዳንኤል ተሬሳ በኮምሽኑ ቢሮ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱም የኢንቨስተር ማህበሩ አባላት በስራ ሂደታቸው ላይ ስላጋጠማቸው ችግሮች፣ ስለፕሮጀክቶቻቸው እንዲሁም መፈታት ስላለባቸው ተግዳሮቶች በሰፊው ውይይት አድርገዋል፡፡ ለተነሱት ሃሳቦችም ከኮምሽኑ ሀላፊዎች ማብራሪያ እንዲሁም የመፍትሄ ሃሳቦች መቅረባቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በመቀጠልም ኮምሽነርዋ ለማህበሩ አባላት የኮምሽኑን ቢሮ እድሳት እና አዲስ ገፅታ ማስጎብኘታቸው ታውቋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here