የቦሌ ሊሚ ኢንደስትሪ ፓርክ የኢንቨስተሮች ማህበር አባላት ዛሬ ከኮምሽነር ለሊሴ ነሜ እና ከምክትል ኮምሽነር ዳንኤል ተሬሳ በኮምሽኑ ቢሮ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱም የኢንቨስተር ማህበሩ አባላት በስራ ሂደታቸው ላይ ስላጋጠማቸው ችግሮች፣ ስለፕሮጀክቶቻቸው እንዲሁም መፈታት ስላለባቸው ተግዳሮቶች በሰፊው ውይይት አድርገዋል፡፡ ለተነሱት ሃሳቦችም ከኮምሽኑ ሀላፊዎች ማብራሪያ እንዲሁም የመፍትሄ ሃሳቦች መቅረባቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
በመቀጠልም ኮምሽነርዋ ለማህበሩ አባላት የኮምሽኑን ቢሮ እድሳት እና አዲስ ገፅታ ማስጎብኘታቸው ታውቋል፡፡





