የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል በጥምር ውጊያ እና ድጋፍ አሰጣጥ ኮርስ ያሰለጠናቸውን አባላት አስመረቀ

0
714

የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል በጥምር ውጊያ እና ድጋፍ አሰጣጥ ኮርስ ከአስር አገራት የተውጣጡ አባላቱን አሰልጥኖ አስመረቀ።

የመከላከያ የውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ ብ/ጀ ጥላሁን አሸናፊ ስልጠናው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን ሰላም እና የተረጋጋ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።

በተጨማሪም በስልጠናው የተገኘውን አቅም በማጎልበት እና ተቀናጅቶ በመስራት ቀጣናውን ከግጭት የፀዳ ማድረግ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

በስልጠናው ያገኙትን አቅም በተግባር አውለው በቀጣናው ሰላም ለማስፈን እና ቀጣናዊ መረጃዎችን በማጋራት የጋራ ግብን ለማሳካት በጋራ እንደሚሰሩ የስልጠናው ተሳታፊዎች መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here